Sun Jun 05 2016 17:35:17 GMT-0700 (Pacific Daylight Time)

This commit is contained in:
weth-04 2016-06-05 17:35:17 -07:00
parent 2d3a4dfba6
commit b996565c69
1 changed files with 1 additions and 9 deletions

View File

@ -1,9 +1 @@
ወንድሞች ሆይ! ወደ እናንተ መምጣታችን ጥቅምየለሽ እንዳልነበረ እናንተው እራሳችሁ ታውቃላችሁ፣ ነገር ግን እንደምታውቁት ቀደም ሲል በፊልጵስዩስ መከራና እንግልት ደረሰብን፡፡ በብዙ ተቃውሞ መካከል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ለመንገር በአምላካችን ድፍረት ነበረን፡፡ የምንመክራችሁ ምክር ከስሕተት ወይም ከእርኩሰት ወይም ከማታለል የመነጨ አይደለም፣ ነገር ግን ወንጌልን በአደራ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር ታማኞች አድርጎ እንደቆጠረን እንዲሁ ሰውን ሳይሆን ልባችንን የሚመረምረውን እርሱን ደስ ለማሰኘት እንናገራለን፡፡ እናንተው እንደምታውቁት መቼም ቢሆን የሽንገላን ቃል አልተጠቀምንም፣ ገንዘባችሁን በመመኘት እንዳልሆነም እግዚአብሔር ምስክር ነው፣ የክርስቶስ ሐዋርያት እንደመሆናችን ልንጠቀምባችሁ መብት ቢኖረንም እንኳን ከእናንተ ወይም ከሌሎች ክብርን ከሰው አልፈለግንም፡፡ ይልቁንም እናት የራስዋን ልጆች እንደምትንከባከብ በመካከላችሁ እንደ የዋህ ሆንን፡፡ ለእናንተ ካለን ብርቱ ፍቅር የተነሳ የእግዚአብሔርን ወንጌል ብቻ ሳይሆን የራሳችንን ሕይወት እንኳን ጨምረን ብንካፈላችሁ ደስ ይለናል፣ ምክንያቱም ለእኛ እጅግ የተወደዳችሁ ሆናችኋልና፡፡ ወንድሞች ሆይ! የእግዚአብሔርን ወንጌል በሰበክንላችሁ ጊዜ በማናችሁም ላይ ሸክም ላለመሆን ቀንና ሌሊት እንደሠራን ድካማችንንና ጥረታችንን ታስታውሳላችሁ፡፡ በእናንተ በምታምኑት መካከል እንዴት በቅድስና፣ በጽድቅና ነቀፋ በሌለበት ኑሮ ራሳችንን እንዳቀረብንላችሁ እግዚአብሔርና እናንተም ጭምር ምስክሮች ናችሁ፣ እናንተው እንደምታውቁት አባት ለራሱ ልጆች እንደሚያደርገው ወደራሱ መንግሥትና ክብር ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እያንዳንዳችሁን መከርናችሁ፣ አበረታታናችሁና መሰከርንላችሁ፡፡
በዚህ ምክንያት እኛ ደግሞ ሳናቋርጥ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፣ የመልዕክቱን ቃል፣ የእግዚአብሔርን ቃል ከእኛ በሰማችሁ ጊዜ እንደሰው ቃል ሳይሆን፣ ነገር ግን እውነት እንደሆነ፣ በእናንተ በምታምኑት ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል ተቀበላችሁት፡፡ እናንተም ወንድሞች ሆይ፣ በይሁዳ የሚኖሩ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑትን የእግዚአብሔር አብያተክርስቲያናት የምትመስሉ ሆናችኋል፣ እነርሱ ከአይሁድ እንደሆነባቸው እናንተ ደግሞ ከገዛ ራሳችሁ ሕዝብ ያንኑ መከራ ተቀብላችኋልና፣ አይሁድ ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን ገደሉ፣ እኛንም አሳደዱን፣ እነርሱ እግዚአብሔርን ደስ አያሰኙትም ነገር ግን ሰውን ሁሉ ይቃወማሉ፡፡ ዘወትር ኀጢአታቸውን ለማብዛትም ይድኑ ዘንድ ለአሕዛብ እንዳንናገር ይከለክሉናል፡፡ ጽኑ ቁጣ መጥቶባቸዋል፡፡ ወንድሞች ሆይ፣ እኛ ለጥቂት ጊዜ በልባችን ሳይሆን በአካል ተለይተናችሁ ነበር፣ በመሆኑም በነበረን ታላቅ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት የተቻለንን ያህል ብርቱ ጥረት አድርገናል፣ ወደ እናንተ ለመምጣት ፈልገን ነበር፣ እኔ ጳውሎስም ከአንድም ሁለት ጊዜ ሞከርኩኝ፣ ነገር ግን ሰይጣን ተከላከለን፡፡ በጌታችን ኢየሱስ መምጣት ፊት የወደፊት መተማመኛችን ወይም ደስታችን ወይም የመክበራችን አክሊል እንደሌሎቹ ሁሉ እናንተ አይደላችሁምን? እናንተ ክብራችንና ደስታችን ናችሁ፡፡
ምዕራፍ 3
ስለዚህ ከዚያ በላይ ልንታገስ ባልተቻለን ጊዜ በአቴንስ ለብቻችን መቅረታችን መልካም እንደሆነ አሰብን፡፡ በእምነታችሁ ያጸናችሁና ያበረታችሁ ዘንድ ወንድማችንንና በክርስቶስ ወንጌል የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልከንላችኋል፣ የላክንላችሁም በእነዚህ መከራዎቻችሁ ማንም እንዳይናወጥ ነው፣ ለዚህ እንደተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁ፡፡ በእርግጥ ከእናንተ ጋር በነበርንበት ወቅት መከራ ልንቀበል እንዳለን አስቀድመን ነግረናችሁ ነበር፣ እንደምታውቁት የሆነውም ይኸው ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ወደፊት ልታገስ ባቃተኝ ጊዜ ምናልባት ፈታኙ ፈትኗችሁና ልፋታችን ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ስለ እምነታችሁ አውቅ ዘንድ ላክሁት፡፡ ጢሞቴዎስ እናንተ ጋ ደርሶ በተመለሰና ስለ እምነታችሁና ፍቅራችሁ የምሥራች ባመጣልን ጊዜ ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ ደግሞ ልናያችሁ እንደምንናፍቅ ሁሉ ልታዩን እንደምትናፍቁ ሲነግረን በዚህ ምክንያት ወንድሞች ሆይ፣ በችግራችንና በመከራችን ሁሉ በእምነታችሁ አማካይነት በእናንተ ተጽናንተናል፡፡ በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ እኛ ደግሞ አሁን በሕይወት እንኖራለን፡፡ በእናንተ ምክንያት በአምላካችን ፊት ስላገኘነው ደስታ ሁሉ ስለ እናንተ ለእግዚአብሔር እንዴት ያለ ምስጋና ማቅረብ እንችል ይሆን? ፊታችሁን ለማየትና በእምነታችሁ የሚጎድላችሁን ለመሙላት ሌሊትና ቀን እጅግ አጥብቀን እንጸልያለን፡፡
ራሱ አምላካችንና አባታችን፣ ጌታችንም ኢየሱስ ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅና፣ እኛ ደግሞ እንደምናፈቅራችሁ ጌታ ለእርስ በርሳችሁና ለሰው ሁሉ የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ያትረፍርፍም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁን ነቀፋ በሌለበት ቅድስና ያጸና ዘንድ ይህንን ያድርግላችሁ፡፡
ምዕራፍ 4
በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፣ እንዴት መመላለስና እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንዳለባችሁ ከእኛ በተማራችሁት መሠረት አሁን እንደምትመላለሱ ከዚህም አብልጣችሁ እንድታደርጉ በጌታ በኢየሱስ እንመክራችኋለን እናደፋፍራችሁማለን፡፡ በጌታ በኢየሱስ በኩል እንዴት ያለውን ትዕዛዝ እንደሰጠናችሁ ታውቃላችሁ፤ ከዝሙት በመራቅ በቅድስና ትኖሩ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ሚስት በቅድስናና በክብር ማግኘት እንዳለበት ታውቃላችሁ፣ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ እንደ አሕዛብ የፍትወት ምኞት አይሁን፣ በዚህ ጉዳይ ማንም አይተላለፍ ወንድሙንም አይበድል፣ ምክንያቱም አስቀድመን እንደነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ ጌታ ስለነዚህ ነገሮች ሁሉ የሚበቀል ነውና፡፡ እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለእርኩሰት አልጠራንም፡፡ ስለዚህ ይህንን የማይቀበል ሰውን ሳይሆን የማይቀበለው ቅዱስ መንፈሱን የሰጣችሁን እግዚአብሔርን ነው፡፡ የወንድማማች መዋደድን በተመለከተ ማንም ሊጽፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፣ እርስ በርስ ስለመዋደድ እናንተው ራሳችሁ በእግዚአብሔር ተምራችኋልና፡፡ በመቄዶንያ ላሉ ወንድሞች ሁሉ ይህንን እንደምታደርጉ እናውቃለን፣ ይሁን እንጂ ወንድሞች ሆይ፣ ከዚህም አብልጣችሁ እንድታደርጉት ደግሞ እንመክራችኋለን፡፡ ደግሞም ልክ እንዳዘዝናችሁ በጸጥታ እንድትኖሩ፣ በራሳችሁ ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩና በገዛ እጆቻችሁ እንድትሠሩ እንለምናችኋለን፡፡ በማያምኑት ዘንድ በአግባብ እንድትመላለሱና ምንም የሚጎድላችሁ እንዳይኖር ይህንን አድርጉ፡፡ ወንድሞች ሆይ፣ ስለወደፊቱ እርግጠኛ መሆን ያልቻሉ እንደሚሆኑት አንቀላፍተው ስላሉት ባለማወቃችሁ ሀዘናችሁ መሪር እንዲሆን አንፈልግም፡፡ ኢየሱስ እንደሞተና እንደተነሳ ካመንን በእርሱ አምነው ያንቀላፉትን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ያመጣቸዋል፡፡ በጌታ ቃል የምንነግራችሁ ይህንን ነው፣ ጌታ በሚመጣበት ጊዜ እኛ ሕያዋን ሆነን የቀረነው በምንም ዓይነት ሁኔታ አስቀድመው ያንቀላፉትን አንቀድማቸውም፡፡ ጌታ ራሱ በታላቅ ድምፅ፣ በመላዕክት አለቃ ድምፅና በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳል፣ በክርስቶስ የሞቱትም አስቀድመው ይነሳሉ፡፡ ከዚያም እኛ ሕያዋን ሆነን የቀረነው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፣ ሁልጊዜም ከጌታ ጋር እንሆናለን፡፡ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በእነዚህ ቃላት ተጽናኑ፡፡
ምዕራፍ 5
ወንድሞች ሆይ፣ አሁን ስለ ጊዜያትና ዘመናት ሊጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፡፡ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ የጌታ ቀንም እንደዚያው እንደሆነ እናንተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁና፡፡ እርጉዝን ሴት የምጥ ህመም እንደሚሆንባት “ሁሉ ሰላምና ደህና ነው” በሚሉበት በዚያን ጊዜ ድንገተኛ ጥፋት ይመጣባቸዋል፣ እነርሱም በምንም መንገድ አያመልጡም፡፡ ወንድሞች ሆይ፣ እናንተ ግን ያ ቀን እንደ ሌባ ይመጣባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፡፡ ሁላችሁም የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁ፡፡ እኛ የሌሊት ወይም የጨለማ ልጆች አይደለንም፡፡ እንግዲያውስ ሌሎች እንደሚያደርጉት አናንቀላፋ፣ ነገር ግን እንንቃ በመጠንም እንኑር፡፡ የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉና የሚሰክሩትም በሌሊት ይሰክራሉ፡፡ የቀን ልጆች እንደመሆናችን በመጠን እንኑር፣ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር፣ የድነታችንን ተስፋ እርግጠኝነትም እንደ ራስ ቁር እንልበስ፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ድነትን ልንቀበል እንጂ እግዚአብሔር ለቁጣ አልመደበንምና፡፡ የነቃን ወይም ያንቀላፋን ብንሆን ከእርሱ ጋር እንድንኖር ስለ እኛ ሞቶአልና፡፡ ስለዚህ አሁን እንደምታደርጉት ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ፣ አንዱም ሌላውን ያንጸው፡፡ ወንድሞች ሆይ፣በመካከላችሁ በትጋት በማገልገል የሚተጉትንና በጌታ የሚያስተዳድሯችሁን፣ የሚመክሯችሁንም እንድታከብሯቸው እንጠይቃችኋለን፡፡ ደግሞም በሥራቸው ምክንያት ከፍ ያለ የፍቅር አክብሮት እንድታሳዩአቸው እንጠይቃችኋለን፡፡ እርስ በርሳችሁ በሰላም ኑሩ፡፡ ወንድሞች ሆይ እንመክራችኋለን፣ ያለ ሥርዓት የሚመላለሱትን አስጠንቅቋቸው፣ ድፍረት ያጡትን አበረታቱአቸው፣ ደካሞችን ደግፉአቸው፣ሁሉንም ታገሱ፡፡ ማንም ስለተደረገበት ክፋት ለሌላው በክፉ እንዳይመልስ ተመልከቱ፣ ነገር ግን ለእርስ በርሳችሁና ለሰው ሁሉ መልካም የሆነውን ለማድረግ ሁልጊዜ ትጉ፡፡ ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፣ ባለማቋረጥ ጸልዩ፣ ስለ ሁሉም ነገር አመስግኑ፣ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ነውና፡፡ መንፈስ ቅዱስን አታዳፍኑ፡፡ ትንቢቶችን አትናቁ፡፡ ሁሉን መርምሩ፣ መልካም የሆነውን ያዙ፣ የትኛውንም ዓይነት ክፋት አስወግዱ፡፡ የሰላም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ መላው መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁና ሥጋችሁ ያለ ነቀፋ ይጠበቅ፡፡ የሚጠራችሁ ታማኝ ነው፣ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል፡፡ ወንድሞች ሆይ፣ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፡፡ ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ አሳሳም ሰላም በሏቸው፡፡ ይህ መልዕክት ለወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አደራ እላችኋለሁ፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡
ወንድሞች ሆይ! ወደ እናንተ መምጣታችን ጥቅምየለሽ እንዳልነበረ እናንተው እራሳችሁ ታውቃላችሁ፣ ነገር ግን እንደምታውቁት ቀደም ሲል በፊልጵስዩስ መከራና እንግልት ደረሰብን፡፡ በብዙ ተቃውሞ መካከል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ለመንገር በአምላካችን ድፍረት ነበረን፡፡