am_1pe_text_ulb/04/01.txt

1 line
398 B
Plaintext

\c 4 \v 1 ክርስቶስ በሥጋው መከራን ስለ ተቀበለ፣ እናንተም በዚሁ ዐላማ ታጥቃችሁ ተነሡ፤ በሥጋው መከራን የሚቀበል ሰው ኀጢአትን ትቶአል። \v 2 እንዲህ ያለው ሰው ከእንግዲህ በሚቀረው ዕድሜ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ምኞት አይኖርም።