am_1pe_text_ulb/05/01.txt

1 line
984 B
Plaintext

\c 5 \v 1 እንግዲህ እኔም ከእነርሱ ጋር ሽማግሌና የክርስቶስ መከራ ምስክር የሆንሁ እንዲሁም ወደ ፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን በመካከላችሁ ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤ \v 2 ስለዚህ፣ በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ የምትጠብቋቸውም ማድረግ ስላለባችሁ በግዴታ ሳይሆን፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ ይሁን፤ ጥቅም ለማግኘት በመስገብገብ ሳይሆን፣ በበጎ ፈቃደኝነት ይሁን፤ \v 3 እንዲሁም በእናንተ ኀላፊነት ሥር ላለው መንጋ መልካም ምሳሌ ሁኑ እንጂ እንደ ዐለቃ በላያቸው አትሠልጥኑ። \v 4 የእረኞች ዐለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ።