am_1pe_text_ulb/04/12.txt

1 line
586 B
Plaintext

\v 12 ወዳጆች ሆይ፤ እንደ እሳት የሚፈትን ብርቱ መከራ ስትቀበሉ፣ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ በመቍጠር አትደነቁ፤ \v 13 ነገር ግን ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታችሁ ታላቅ እንዲሆን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በመሆናችሁ ሐሴት አድርጉ። \v 14 ስለ ክርስቶስ ስም ብትሰደቡ፣ የክብር መንፈስ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ስለሚያርፍ ቡሩካን ናችሁ።