am_1pe_text_ulb/04/03.txt

1 line
834 B
Plaintext

\v 3 አሕዛብ ፈልገው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋ ምኞት፣ በስካር፣ ቅጥ ያጣ ፈንጠዝያ፣ በጭፈራና ርኵስ ከሆነ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና። \v 4 እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ከአነርሱ ጋር አለመተባበራችሁ እንግዳ ሆኖባቸው ስለ እናንተ ክፉ ያወራሉ። \v 5 ነገር ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ። \v 6 ወንጌል ለሙታን የተሰበከው በዚህ ምክንያት ነው፤ በሥጋቸው እንደ ሰው ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በመንፈስ ይኖራሉ።