am_1pe_text_ulb/03/21.txt

1 line
557 B
Plaintext

\v 21 ይህም ውሃ አሁን እናንተን የሚያድነው የጥምቀት ምሳሌ ነው፤ ይህ ጥምቀት የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ ሳይሆን ንጹሕ ኅሊናን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልመና ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው፤ \v 22 እርሱ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ አለ፤ መላእክት፣ ሥልጣናትና ኀይላትም ተገዝተውለታል።