am_1ki_tn/16/18.txt

30 lines
3.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ከተማይቱ ተወስዳ/ተይዛ ነበር\n",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"ይኸውም ዖምሪ እና ሰራዊቱ ከተማይቱን ያዟት\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በያህዌ ፊት ክፉ የነበረውን\n",
"body": "የያህዌ እይታ የሚለው የሚወክለው የያህዌን ፍርድ ነው፡፡ \"በያህዌ ፍርድ/ሚዛን ክፉ የሆነውን\" ወይም \"ያህዌ ክፉ ብሎ የሚቆጥረውን\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በኢዮርብዓም መንገድ መሄድ\n",
"body": "መሄድ የሚወክለው ማድረግን ነው፡፡ \"ኢዮርብዓም ያደረገውን ተመሳሳይ ነገር አንተም አደረግህ\" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እስራኤልን ወደ ኃጢአት መምራት \n",
"body": "ሰዎች አንድ ነገር እንዲያደርጉ መምራት የሚገልጸው አንድ ነገር እንዲፈጸሙ ተጽዕኖ ማሳደርን ነው፡፡ \"እስራኤል ኃጢአት እንዲያደርግ ተጽዕኖ ማሳደር\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እርሱ የፈጸመው ክህደት\n",
"body": "ክህደቱ የሚያመለክተው ዘምሪ የእስራኤልን ንጉሥ ኤላን ለመግደል ያደረገውን ሴራ ነው፡፡ የዚህ ሀሳብ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ \"በንጉሥ ኤላ እንዴት ሴራ ፈጸመ\" ወይም \"የእስራኤልን ንጉሥ እንዴት እንደ ገደለ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ) \n"
},
{
"title": "የእስራኤል ነገሥታት ስራዎች በተጻፈበት መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ አይደለምን?\n",
"body": "ይህ ጥያቄ የዋለው አንባቢያን ስለ ዘምሪ ያለው መረጃ በዚነህ ሌሎች መጽሐፍት ውስጥ እንደሚገኝ ለማሳወቅ ወይም ለማስታወስ ነው፡፡ ይህ በ1ነገሥት 14፡29 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ ቃለ ምልልሳዊው ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"እነዚህ ታሪኮች የእስራኤል ነገሥታት የፈጸሟቸው ድርጊቶች በተጻፉባቸው መጽሐፍት ውስጥ ተጽፈዋል፡፡\" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእስራኤል ነገሥታት …የተጻፈ አይደለምን?\n",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"አንድ ሰው ይህንን የእስራኤል ነገሥታት ድርጊቶች በተጻፈበት መጽሐፍ ጽፎታል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)\n"
}
]