am_1ki_tn/16/07.txt

18 lines
1.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል መጣ",
"body": "ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለህዝቡ አዲስ ነገርን ለማስተዋወቅ የሚውል ነው፡፡ ይህ በ1 ነገሥት 6፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ይህን መልዕክት ተናገረ\" ወይም \"ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በያህዌ እይታ ሲታይ እርሱ ያደረገውን ክፉ የሆነውን ሁሉ ",
"body": "የያህዌ እይታ የሚለው የሚወክለው የያህዌን ፍርድ ነው፡፡ \"ባኦስ ያደረገው በያህዌ ፍርድ/ሚዛን ክፉ የሆነውን\" ወይም \"ባኦስ ያደረገውን ያህዌ ክፉ ብሎ የሚቆጥረውን ነገር ሁሉ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እርሱ እንዲቆጣ ለማነሳሳት",
"body": "\"ቁጣ\" የሚለው ረቂቅ ስም \"መቆጣት\" በሚለው ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"ያህዌ በጣም እንዲቆጣ የሚያደርግ\" ወይም \"እግዚአብሔርን በጣም የሚያስቆጣ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእጆቹ ስራ",
"body": "እዚህ ስፍራ ባኦስ የተወከለው በ\"እጆቹ\" ነው፡፡ ይህ የሚናገረው ድርጊቶቹን ሁሉ እንደ እርሱ \"ስራ\" አድርጎ ነው፡፡ \"ባኦስ ባደረጋቸው ነገሮች\" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]