am_1ki_text_ulb/21/05.txt

1 line
871 B
Plaintext

\v 5 ሚስቱም ኤልዛቤል ወደ እርሱ ቀርባ እንደዚህ ያበሳጨህ ነገር ምንድን ነው? ስለምንስ ምግብ አትበላም? ስትል ጠየቀችው፡፡ \v 6 እርሱም እኔን ያበሳጨኝ ከናቡቴ ያገኘሁት መልስ ነው፤ ይኸውም የእርሱን የወይን ተክል ቦታ እንድገዛ ወይም ከፈለገ ልዋጩን እንድሰጠው ብጠይቀው የወይን ተክል ቦታውን አልሰጥህ ብሎ አናደደኝ ሲል መለሰላት፡፡ \v 7 ኤልዛቤልም እንግዲህ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ሆነህ ሳለህ እንደዚህ መሆን ይገባሃልን? ይልቅስ ተነሥ ተደሰት፤ እህል ውሃም ቅመስ፡፡ እኔ የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ እንድታገኝ አደርጋለሁ አለችው፡፡