am_1ki_text_ulb/20/41.txt

1 line
718 B
Plaintext

\v 41 ነቢዩ ፊቱ የተሸፈነበትን ጨርቅ ፈጥኖ አወለቀ፤ ንጉሡም ይህ ሰው ከነቢያት ወገን አንዱ መሆኑን ወዲያውኑ አወቀ፡፡ \v 42 ነቢዩም ንጉሡን እንዲህ አለው፡- እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ እኔ ይገደል ብዬ የፈረድኩበት ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል፡፡ \v 43 ስለዚህ ንጉሡ እያዘነና እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ወደ ሰማርያ ተመልሶ ሄደ፡፡