\v 37 ስለዚህ ንጉሥ አክዓብ ሞተ፤ ሬሳውም ወደ ሰማርያ ተወስዶ ተቀበረ፡፡ \v 38 ሠረገላውም በሰማርያ ኩሬ ታጠበ፤ እግዚአብሔርም አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ደሙን ውሾች ላሱት፤ በዚያም ኩሬ ሴተኛ አዳሪዎች ታጠቡበት፡፡