am_1ki_text_ulb/22/31.txt

1 line
595 B
Plaintext

\v 31 የሶርያ ንጉሥም በንጉሡ ላይ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ ብሎ ለሠላሳ ሁለቱ የሠረገላ ጦር አዛዦች ትአዛዝ አስተላለፈ፡፡ \v 32 ስለዚህ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ በርግጥ እርሱ የእስራኤል ንጉሥ ነው ብለው በእርሱ ላይ አደጋ ሊጥሉበት ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥም በጮኸ ጊዜ፣ \v 33 እርሱ የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን በማረጋገጥ በእርሱ ላይ አደጋ ከመጣል ተመለሱ፡፡