am_1ki_text_ulb/22/29.txt

1 line
581 B
Plaintext

\v 29 ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ወደ ገለዓድ ምድር ወደምትገኘው ራሞት ከተማ ለመዋጋት ሄዱ፡፡ \v 30 አክዓብም ኢዮሣፍጥን ወደ ጦርነት ለመሄድ ስንነሣ እኔ ሌላ ሰው መስዬ ለመታየት ተራ ልብስ እለብሳለሁ፣ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ አለው፡፡ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ሌላ ልብስ ለብሶ ማንነቱን በመሰወር ዘመተ፡፡