am_1ki_text_ulb/22/13.txt

1 line
997 B
Plaintext

\v 13 ሚክያስን ለመጥራት ሄዶ የነበረው መልእክተኛ በዚሁ ጊዜ ሚክያስን ሌሎቹ ነቢያት በሙሉ ንጉሥ አክዓብ ድል የሚያደርግ መሆኑን የሚያረጋግጥ የትንቢት ቃል ተናግረዋል፤ ስለዚህ አንተም እንደእነርሱ ብታደርግ ይሻልሃል አለው፡፡ \v 14 ሚክያስ ግን እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ቃል ብቻ እንደምናገር በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ! ሲል መለሰለት፡፡ \v 15 ሚክያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ፊት በቀረበ ጊዜ ንጉሡ፣ ሚክያስ ሆይ፣ ንጉሥ ኢዮሣፍጥና እኔ ወደ ራሞት ሄደን ጦርነት እንክፈት ወይስ እንተው? ሲል ጠየቀው፡፡ ሚክያስም ዘምተህ አደጋ ጣልባት ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ ሲል መለሰለት፡፡