am_1ki_text_ulb/18/12.txt

1 line
774 B
Plaintext

\v 12 እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርህን ለአከዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ፡፡ \v 13 ደግሞስ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ስታስገድል በነበረችበት ጊዜ አንድ መቶ የሚሆኑትን ነቢያት ከሁለት በመክፈል ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ እህልና ውሃ በማቅረብ ስመግባቸው መኖሬን አልሰማህምን?