am_1ki_text_ulb/18/03.txt

1 line
572 B
Plaintext

\v 3 ስለዚህ ንጉሥ አክዓብ የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን አብድዩን ጠራው፤ አብድዩ እግዚአብሔርን የሚፈራ መንፈሳዊ ሰው ነበር፡፡ \v 4 ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ታስገድል በነበረበት ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ መግቦአቸው ነበር፡፡