am_1ki_text_ulb/17/22.txt

1 line
600 B
Plaintext

\v 22 እግዚአብሔርም የኤልያስን ጸሎት ሰማ፤ የልጁም እስትንፋስ እንደገና ተመልሶለት ዳነ፡፡ \v 23 ኤልያስም ልጁን ከሰገነት ወደ ምድር ቤት አውርዶ ለእናቱ ሰጣትና እነሆ ልጅሽ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሶአል! አላት፡፡ \v 24 እርስዋም እነሆ አንተ የእግዚአብሔር ሰው መሆንህንና እግዚአብሔርም በአንተ አማካይነት የተናገረው እውነት መሆኑን አሁን ዐወቅሁ! ስትል መለሰችለት፡፡