am_1ki_text_ulb/17/19.txt

1 line
869 B
Plaintext

\v 19 ኤልያስም ልጅሽን ወደ እኔ አምጪው አላት፡፡ ልጁንም ከዕቅፍዋ ወስዶ እርሱ ወደሚኖርበት ሰገነት አውጥቶ በአልጋው ላይ አጋደመው፡፡ \v 20 ከዚህ በኋላ ኤልያስ ድምፁን ከፍ በማድረግ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ስለምን በዚህች ባልዋ በሞተባት ሴት ላይ ይህን የመሰለ አሠቃቂ ነገር አደረግህ? እርስዋ እኔን በማስተናገድ ታላቅ ቸርነት አድርጋልኛለች፤ ታዲያ አንተ ስለምን ልጅዋ እንዲሞት አደረግህ ሲል ጸለየ፡፡ \v 21 ከዚህ በኋላ ኤልያስ በልጁ ላይ ሦስት ጊዜ ተዘርሮ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ይህን ልጅ ከሞት አስነሣው ሲል ጸለየ፡፡