am_1ki_text_ulb/17/11.txt

1 line
1.1 KiB
Plaintext

\v 11 ውሃም ልታመጣለት በመሄድ ላይ ሳለች ወዲያውኑ ጠርቶ እባክሽ በተጨማሪ ትንሽ እንጀራ አምጪልኝ አላት፡፡ \v 12 እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፡- ምንም እንጀራ እንደሌለኝ በአምላክህ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ በዱቄት ዕቃዬ ውስጥ ካለችው ከአንድ እፍኝ ዱቄትና በማሰሮዬ ውስጥ ካለችው ከጥቂት የወይራ ዘይት በቀር ምንም የለኝም፤ ወደዚህ የመጣሁት ትንሽ እንጨት ለቃቅሜ ቤቴ በመመለስ ይህችኑ ትንሽ ዱቄት ለእኔና ለልጄ ለመጋገር ነው፤ ይህችም የመጨረሻ ምግባችን ናት፤ ከዚያ በኋላ ይህችኑ በልተን እንሞታለን፡፡ \v 13 ኤልያስም እንዲህ አላት፣ አይዞሽ አትጨነቂ፤ ሄደሽ ምግብሽን አዘጋጂ፤ አስቀድመሽ ግን ከዚች ካለችሽ ዱቄት ለእኔ ትንሽ እንጎቻ ጋግረሽ አምጪልኝ፤ የቀረውንም ለራስሽና ለልጅሽ ጋግሪው፡፡