am_1ki_text_ulb/15/18.txt

1 line
862 B
Plaintext

\v 18 ከዚያም ንጉሥ አሳ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ የተረፈውን ወርቅና ብር ሁሉ ወሰደ፡፡ እርሱም በአገልጋዮቹ እጅ በደማስቆ ከተማ ለነበረው የአዚን ልጅ የጣብሪሞን ልጅ ለሆነው ለሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ ስጦታ አድርጎ ላከለት፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፡- \v 19 የእኔ አባትና የአንተ አባት ያደርጉት በነበረው ዓይነት በመካከላችን ቃል ኪዳን ይኑር፡፡ እነሆ ብርና ወርቅ ስጦታ እንዲሆንህ ልኬልሃለሁ፡፡ የእሰራኤል ንጉሥ ባኦስ እኔን እንዲለቀኝ ቀደም ሲል ከእርሱ ጋር ያደረግኸውን ቃል ኪዳን አሁን እንድታቋርጥ ይሁን፡፡