am_1ki_text_ulb/15/01.txt

1 line
622 B
Plaintext

\c 15 \v 1 1 ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት አቢያ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ \v 2 እርሱም በኢየሩሳሌም ሦስት ዓመት ነገሠ፡፡ የእናቱ ስም ማዕካ ሲሆን፣ እርስዋም የአቤሴሎም ልጅ ነበረች፡፡ \v 3 አቢያም እንደ ቀደሙት አባቶቹና እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ ፍፁም ታማኝ ሆኖ አልተገኘም፡፡ አባቱ ሮብዓም ይፈፅመው የነበረውን ኃጢአት ሁሉ መሥራት ቀጠለ፡፡