am_1ki_text_ulb/11/31.txt

1 line
1011 B
Plaintext

\v 31 ኢዮርብዓምንም እንዲህ አለው፤ የእስራኤል አምላክ እግዚያብሔር እንዲህ ይላል፡- ‹‹ዐሥሩን ቁራጭ ለራስህ ውሰድ፤ ‹መንግሥትን ከሰለሞን ወስጄ ዐሥሩን ነገድ ለአንተ እሰጥሃለሁ፣ \v 32 ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰለሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ፡፡ \v 33 ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን አማልክትን፡- አስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፣ ካሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሞሎክ ተብሎ የሚጠራውን የአሞናውያን አምላክ ስላመለከ ነው፡፡ አባቱ ዳዊት እንዳደረገ በፊቴ ትክክል የሆነውን፣ ሕጎቼንና ትእዛዞቼንም አልጠበቀም፡፡