am_1ki_text_ulb/11/23.txt

1 line
909 B
Plaintext

\v 23 እንደገናም እግዚአብሔር ረዞን ተብሎ የሚጠራውን የኤሊዓዳ ልጅ በሰሎሞን ላይ ሌላ ጠላት አድርጎ አስነሣበት፡፡ ረዞን የጾባ ንጉሥ ከነበረው ከጌታው ከዞአብ ንጉሥ ከሀዲድዔዚር ኮብልሎ ነበር፡፡ \v 24 ዳዊት ሀዲድዔዚርን ድል ባደረገበት ጊዜ፣ ረዞን ለራሱ ጦር ሰብስቦ የጥቂት ኃይል አለቃ ሆኖ ነበር፡፡ የረዞን ጦር ወደ ደማስቆ ሄደው እዚያ መኖር ጀመሩ፤ በኋላም ደማስቆን ተቆጣጠረ፡፡ \v 25 በሰሎለሞን ዘመነ መንግሥት ሁሉ ሀዳድ ካደረሰበት ችግር በተጨማሪ ረዞን የእስራኤል ጠላት ነበር፡፡ ስለዚህ ረዞን በሶርያ ላይ ገዢ ሆኖ በእስራኤል ላይ ጠላትነቱን ቀጠለ፡፡