am_1ki_text_ulb/11/11.txt

1 line
698 B
Plaintext

\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- ከእኔ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ስላፈረሰክና ሕጌንም ስላልፈጸምክ መንግሥትህን ከአንተ ወስጄ ከአገልጋዮችህ ለአንዱ እሰጣለሁ፡፡ \v 12 ይሁን እንጂ ለአባትህ ለዳዊት ስል ይህን የማደርገው አንተ ባለህበት ዘመን ሳይሆን በልጅህ መንግሥት ጊዜ ይሆናል፡፡ \v 13 ሆኖም ሁሉንም መንግሥት አልወስድም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለመረጥኩት ከተማ ለኢየሩሳሌም ስል ለልጅህ አንዱን ነገድ እሰጠዋለሁ፡፡