am_1ki_text_ulb/10/23.txt

1 line
620 B
Plaintext

\v 23 ንጉሥ ሰሎሞን ከምድር ነገሥታት ሁሉ የሚበልጥ ሀበታምና ጥበበኛ ነበር፤ \v 24 በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎችም ሁሉ እግዚአብሔር የሰጠውን ጥበብ የሞላበትን ንግግር ይሰሙ ዘንድ ወደ እርሱ መምጣት ይፈልጉ ነበር፡፡ \v 25 ወደ እርሱም የሚመጡት ሁሉ የብርና የወርቅ፣ የልብስ፣ የጦር መሣሪያዎች፣ የሽቶ፣ የፈረሶች የበቅሎዎች ስጦታዎች ያመጡለት ነበር፤ ይህም በየዓመቱ የሚደረግ ነበር፡፡