am_1ki_text_ulb/10/21.txt

1 line
630 B
Plaintext

\v 21 በሰሎሞን ዘመን ብር ምንም ዋጋ ስላልነበረው ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዋንጫዎች ሁሉና የሊባኖስ ጫካ ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች በሙሉ ከንጹሕ ወርቅ እንጂ ከብር አልተሠሩም፤ \v 22 ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱ በየሦስት ዓመት ወርቅ፣ ብር፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር፡፡