am_1ki_text_ulb/10/18.txt

1 line
787 B
Plaintext

\v 18 እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን ከዝሆን ጥርስ አንድ ትልቅ ዙፋን አሠርቶ በንጹሕ ወርቅ አስለበጠው፡፡ \v 19 ወደ ዙፋኑ መወጣጫ ስድስት ደረጃዎች ነበሩ፤ የዙፋኑ ጀርባ ራስጌው ክብ ነበር፤ በዙፋኑ ግራና ቀኝ የክንድ ማሳረፊያዎች ነበሩት፤ በክንድ ማሳረፊያዎቹ ጎን አንዳንድ የአንበሳ ምስሎች ቆመው ነበር፡፡ \v 20 በእያንዳንዱ ደረጃ በሁለት በኩል አንዳንድ የአንበሳ ምስል በድምሩ ዐሥራ ሁለት የአንበሳ ምስሎች ቆመዋል፡፡ ይህን የመሰለ ዙፋን በሌላ በየትኛውም አገር ተሠርቶ አያውቅም ነበር፡፡