am_1ki_text_ulb/10/11.txt

1 line
706 B
Plaintext

\v 11 ከኦፊር ወርቅ ብዙ ያመጡለት የኪራም መርከቦች ከዚያው ከኦፊር ብዙ የሰንደል እንጨትና የከበረ ዕንቁ አምጥተውለት ነበር፡፡ \v 12 ሰሎሞን ከዚሁ ከሰንደል እንጨት የቤተ መቅደሱንና የቤተ መንግሥቱን መከታዎች፤ መዘምራን የሚያገለግሉባቸውን በገናዎችና መሰንቆዎች አሠራ፤ ይህም የሰንደል እንጨት ወደ እስራኤል አገር ከመጣው የሰንደል እንጨት ሁሉ የሚበልጥ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ይህን የመሰለ የሰንደል እንጨት ከቶ ታይቶ አይታወቅም፡፡