am_1ki_text_ulb/10/03.txt

1 line
894 B
Plaintext

\v 3 እርሱም ላቀረበችለት ጥያቄ ሁሉ መልስ ሰጣት፤ ከጠየቀችው ሳይመልስላት የቀረ ምንም ዓይነት እንቆቅልሽ አልነበረም፡፡ \v 4 ንግሥተ ሳባ ጥበብ የተሞላበትን የሰሎሞንን አነጋገር አዳመጠች፤ የሠራውንም ቤተ መንግሥት አየች፡፡ \v 5 በሰሎሞን ገበታ ላይ የሚቀርበውን የምግብ ዓይነት፣ የመኳንንቱን መኖሪያ አካባቢዎች፣ የቤተ መንግሥቱን አሠራርና አደረጃጃት፣ የደንብ ልብሳቸውን ዓይነት፣ በግብዣ ጊዜ የሚያገለግሉትን አሳላፊዎችና በቤተ መቅደስም ያቀረባቸውን መሥዋዕቶችን ሁሉ ተመለከተች፤ በዚህም ሁሉ የተሰማት አድናቆት ከጠበቀቸው በላይ ሆነባት፤