am_1ki_text_ulb/09/26.txt

1 line
578 B
Plaintext

\v 26 እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን በኤዶም ምድር በቀይ በሕር ዳርቻ በምትገኘው በኤላት አጠገብ ባለችው በዔጽዮን ጋብር መርከቦችን ሠራ፡፡ \v 27 ንጉሥ ኪራምም ከሰሎሞን ሰዎች ጋር የሚያገለግሉ የሠለጠኑ መርከበኞችን ላከለት፡፡ \v 28 እነርሱም በመርከብ ተጉዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ይዘውለት መጡ፡፡