am_1ki_text_ulb/09/15.txt

1 line
843 B
Plaintext

\v 15 ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና ቤተ መንግሥቱን፣ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር የሠሩለትና ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጎድጓዳ ስፍራ መጥተው ያስተካከሉለት የጉልበት ሥራ ዋጋ ነበር፤ እንዲሁም ሐጸር፤ መጊዶናጊዜር ተብለው የሚጠሩ ከተሞችም እንዲሠሩለት አደረገ፡፡ \v 16 ቀደም ሲል የግብጽ ንጉሥ ፈረዖን በጌዜር ላይ አደጋ ጥሎ፣ ነዋሪዎችዋን ከነዓናውያንን ገድሎ ከተማይቱንም አቃጥሎ በቁጥጥሩ ሥር አድርጓት ነበር፤ ከዚያም በኋላ ለሴት ልጁ ለሰሎሞን ሚስት እንደ ስጦታ ሰጣት፡፡