am_1ki_text_ulb/09/08.txt

1 line
923 B
Plaintext

\v 8 ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ ይህንን አይተው በመደንገጥ እግዚአብሔር ይህንን አገርና ይህንን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ በማለት ይሳለቁበታል፡፡ \v 9 ራሳቸው በሚሰጡት መልስ፣ የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎች አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው የሚል ይሆናል፡፡