am_1ki_text_ulb/08/65.txt

1 line
737 B
Plaintext

\v 65 በዚያ ቤተ መቅደስ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ ባጠቃላይ ዐሥራ አራት ቀኖች የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝበ እጅግ ብዙ ነበር፡፡ \v 66 በሚቀጥለው ቀን ሰሎሞን ሕዘቡን ሁሉ አሰናበተ፤ ሁሉም ሰሎሞንን መረቁ እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ፣ ለእስራኤል ስለ አደረገው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ብሎአቸው ወደየቤታቸው ሄዱ፡፡