am_1ki_text_ulb/08/62.txt

1 line
520 B
Plaintext

\v 62 ስለዚህ ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፡፡ \v 63 ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ሃያ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፡፡ በዚህም ዓይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱን ለእግዚአብሔር የተለየ አድርገው ቀደሱት፡፡