am_1ki_text_ulb/08/41.txt

1 line
873 B
Plaintext

\v 41 በተጨማሪም የሕዝብህ የእስራኤል ወገን ያልሆነ፣ የውጪ አገር ሰው ከስምህ የተነሣ ከሩቅ ቢመጣ፤ \v 42 ስለስምህ ገናናነት፣ ስለታላቁ እጅህና ከፍ ስላለው ክንድህ ሰምተው፣ በዚህ ቤተ መቅደስ ቢመጡና ቢጸልዩ፣ \v 43 ከምትኖርበት ከሰማይ ሆነህ የዚያን ሰው ጸሎት ስማ፤ እንድታደርግለት የሚለምንህንም ሁሉ ፈጽምለት፤ ሕዝብህ እስራኤላውያን እንደሚያደርጉት በመላው ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች አንተን በማወቅ እንዲታዘዙህና እንዲያከብሩህ አድርግ፣ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ይህ እኔ የሠራሁት ቤተ መቅደስ የአንተ ስም የሚጠራበት መሆኑን ያውቃሉ፡፡