am_1ki_text_ulb/08/35.txt

1 line
794 B
Plaintext

\v 35 የእስራኤል ሕዝብ በደል ሠርተው አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት ዝናብ እንዳይዘንብላቸው አድርገህ በምትቀጣቸው ጊዜ በፈጸሙት በደል በመጸጸት ፊታቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰው በትሕትና ቢለምኑህ፤ \v 36 አንተ በሰማያት ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፣ በልብ ቅን የሆነውንም ነገር ማድረግ ይችሉ ዘንድ አስተምራቸው፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሆይ፣ ለዘለዓለም ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።