am_1ki_text_ulb/08/06.txt

1 line
737 B
Plaintext

\v 6 ከዚህም በኋላ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል፣ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ወደ ቦታው አምጥተው በኪሩቤል ክንፎች ሥር አኖሩት፡፡ \v 7 የተዘረጉ የኪሩቤል ክንፎችም የታቦቱን መሸከሚያ መሎጊያዎች ሸፍነው ነበር፡፡ \v 8 መሎጊያዎቹ ረጃጅሞች ስለ ሆኑ ጫፎቻቸው በቤተ መቅደሱ ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ለሚቆም ሰው ሁሉ በግልጽ ይታዩ ነበር፤ በሌላ አቅጣጫ የሚቆም ግን አያያቸውም፡፡ እስከ ዛሬም እዚያው ይገኛል፡፡