am_1ki_text_ulb/08/03.txt

1 line
663 B
Plaintext

\v 3 መሪዎቹ ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜም ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አንሥተው ተሸከሙ፡፡ \v 4 ካህናቱም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት፣ የመገናኛ ድኳንና በድንኳኑም ውስጥ የነበሩትን ንዋያተ ቅዱሳት ሁሉ አምጥተው ወደ ቤተ መቅደስ አገቡ፡፡ \v 5 ንጉሥ ሰሎሞንና መላው የእስራኤል ሕዝብ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ተሰበሰቡ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቆጠር የማይችል ብዙ በጎቸና የቀንድ ከብት መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡