am_1ki_text_ulb/06/19.txt

1 line
535 B
Plaintext

\v 19 ሰሎሞንም ከቤተ መቅደሱ ውስጥ በስተኋላ በኩል የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የሚቀመጥበት ውስጣዊ ክፍል አዘጋጀ፡፡ \v 20 ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፣ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፣ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር ሲሆን፣ በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበጠ ነበር፡፡