am_1ki_text_ulb/06/16.txt

1 line
870 B
Plaintext

\v 16 ውስጣዊ ክፍል ከቤተ መቅደሱ በስተ ኋላ ገባ ብሎ ተሠራ፣ የእርሱም ርዝመት ዘጠኝ ሜትር ሲሆን ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተከፈለ ነበር፤ ይህንን ክፍል ቅድሰተ ቅዱሳን ውስጠኛ ክፍል እንዲሆን ነው፡፡ \v 17 ከቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት የሚገኘውም የተቀደሰ ክፍል ርዝመት አርባ ክንድ ነበር፡፡ \v 18 የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሳንቃዎች በአበባ እንቡጦችና በፈኩ አበባዎች ቅርጽ አጊጠው ነበር፤ ውስጡም ሁሉ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ ስለ ተለበጠ የግንቡ ድንጋዮች አይታዩም ነበር፡፡