am_1ki_text_ulb/06/09.txt

1 line
580 B
Plaintext

\v 9 በዚህ ሁኔታ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሕንፃ ሥራ ፈጸመ፤ ጣራውንም ከውስጥ በኩል ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ አግዳሚ ሠረገላና ጠርብ ቤቱን ሸፈነው፡፡ \v 10 የእያዳንዱ ፎቅ ቁመት አምስት ክንድ ከፍታ ሆኖ ከውጪ በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ ተጠግቶ የተሠራው ባለ ሦስት ፎቅ ተጨማሪ ሕንፃ ከዋናው ሕንፃዎች ከሊባኖስ ዛፍ በተሠሩት አግዳሚ ወራጆች የተያያዘ ነበር፡፡