am_1ki_text_ulb/05/10.txt

1 line
664 B
Plaintext

\v 10 በዚህ ዓይነት ኪራም ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖሱን ዛፍና የዝግባ ግንድ ሁሉ ሰጠው፡፡ \v 11 ሰሎሞንም በበኩሉ ለኪራም ቤተ ሰቦች ቀለብ የሚሆን ሃያ ሺህ መስፈሪያ ስንዴና ሃያ መስፈሪያ ንጹሕ ዘይት ሰጠ፡፡ ይህንንም በየዓመቱ ይሰጥ ነበር፡፡ \v 12 እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብ ሰጠው፤ በሰሎሞንና በኪራም መካከል ሰላም ነበር፤ ሁለቱም የጋራ ስምምነት አደረጉ፡፡