am_1ki_text_ulb/04/29.txt

1 line
723 B
Plaintext

\v 29 እግዚአብሔር ለሰሎሞን አጅግ አስደናቂ የሆነ ጥበብንና አስተተዋይነትን እንዲሁም እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ወሰን የማይገኝለትን ዕውቀት ሰጠው፡፡ \v 30 የሰሎሞንም ጥበብ ከምሥራቅ አገርና ከግብፅም ጥበበኞች እጅግ የላቀ ነበረ፡፡ \v 31 እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ፤ ከኢይዝራኤላዊው ኤታን፣ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሮማን ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጎረቤት ሕዘቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ፡፡