am_1ki_text_ulb/04/24.txt

1 line
794 B
Plaintext

\v 24 ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለው ምድር ሁሉ ከቲፍሳ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታት ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጎረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር፡፡ \v 25 በኖረበትም ዘመን ሁሉ ከዳር እስከ ቤርሳቤህ ድረስ መላው የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ያለ ስጋት በሰላም ይኖር ነበር፤ እያንዳንዱ ቤተ ሰብ ለራሱ የሆነ የወይን ተክልና የበለስ ዛፍ ስለ ነበረው በእነዚህ ተክሎች ጥላ ሥር ያርፍ ነበር፡፡