am_1ki_text_ulb/04/20.txt

1 line
1.1 KiB
Plaintext

\v 20 የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ እየበሉና እየጠጡ ዘወትር ደስ እየተሰኙ ነበር፡፡ \v 21 የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፣ ከዚያም አልፎ እስከ ግብፅ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር፡፡ \v 22 ሰሎሞንም በየቀኑ ለቀለብ የሚሆን አምስት ሺህ ኪሎ ግራም ያህል ምርጥ ዱቄት፤ ዐሥር ሺህ ኪሎ ግራም ያህል ነበር፡፡ \v 23 በበረት ውስጥ እየተመገቡ የደለቡ ዐሥር ሰንጋዎችና በግጦሽ መስክ ተሰማርተው የተመገቡ ሃያ ፍሪዳዎች፣ አንድ መቶ በጎች፤ ከዚህም ሌላ አጋዘኖች፣ የሜዳ ፍየሎች፤ ሚዳቆዎችና ምርጥ ወፎች ያስፈልጉት ነበር፡፡