am_1ki_text_ulb/04/11.txt

1 line
1.2 KiB
Plaintext

\v 11 ጣፋት የተባለችውን የሰሎሞንን ሴት ልጅ አግብቶ የነበረው ቤን አሚናዳብ የመላው የዶር ግዛት አስተዳዳሪ፤ \v 12 በዓና የተባለው የአሒሉድ ልጅ፡-የታዕናክና የመጊዶ ከተሞች፤ እንዲሁም በቤትሳን አጠገብ ያለው ግዛት በሙሉ በጸርታን ከተማ አጠገብ ያለው ግዛትና በኢይዝራኤል ከተማ በስተደቡብ ያለው ግዛት፤ እንዲሁም አቤልመሖላና ዮቅምዓም ተብለው እስከሚጠሩት ከተሞች ድረስ ያለው ግዛት ሁሉ አስተዳዳሪ፤ \v 13 በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የኢያዕር ጎሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፤ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጥር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስልሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ፤ \v 14 አሒናዳብ የተባለው የዔዶ ልጅ፡- የመሃናይም ክፍለ አገር ገዢ፤