am_1ki_text_ulb/04/01.txt

1 line
667 B
Plaintext

\c 4 \v 1 ንጉሡ ሰሎሞን በመላው አስራኤል ላይ ነግሦ ነበር። \v 2 ንጉሡም የሾማቸው ባለሥልጣኖች እነዚህ ናቸው። እነርሱም፡- ዓዛርያስ የተባለው የሳዶቅ ልጅ፡- ካህን ነበር። \v 3 ኤልያፍና አኪያ የተባሉ የሴባ ልጆች የቤተ መንግሥት ጻሐፊዎች ነበሩ። ኢዮሣፍጥ የተባለው የአሒሉድ ልጅ ታሪክ ጻሐፊና የመዛግብት ኃላፊ ነበር። \v 4 በናያስ የተባለው የዮዳሄ ልጅ የጦር ሠራዊት አዘዥ ነበር። ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ።