am_1ki_text_ulb/02/19.txt

1 line
727 B
Plaintext

\v 19 ስለዚህ ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሡ ገባች። ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት። እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት። \v 20 እርስዋም እንድትፈጽምልኝ የምጠይቅህ አንድ ትንሽ ጉዳይ አለኝ፣ እባክህ እምቢ በማለት አታሳፍረኝ አለችው። ንጉሡም እናቴ ሆይ አላሳፍርሽምና ጠይቂኝ አላት። \v 21 እርስዋም ወንድምህ አዶንያስ አቢሳን እንዲያገባት ፍቀድለት አለችው።