am_1ki_text_ulb/02/01.txt

1 line
997 B
Plaintext

\c 2 \v 1 ዳዊት የሚሞትበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ እንዲህ ሲል አዘዘው፤ \v 2 እነሆ እኔ ሰው ሁሉ እንደሚሞት የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እንግዲህ በርታ ቆራጥ ሰው ሁን፡፡ \v 3 አምላክህ እግዚአብሔር እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፣ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማናቸውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግ ትእዛዝ፣ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፡፡ \v 4 በዚህ ሁሉ ታዛዥ ሆነው ቢኖሩ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም ብሎ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል፡፡