am_1ki_text_ulb/01/41.txt

1 line
587 B
Plaintext

\v 41 አዶንያስና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንግዶች ሁሉ ምግባቸውን እንደጨረሱ ይህንን ድምፅ ሰሙ። ኢዮአብ የእምቢልታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ፣ “ይህ በከተማ ውስጥ የሚሰማው ሁካታ ምንድን ነው?” አለ። \v 42 እርሱ ገና በመናገር ላይ እያለ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ። አዶንያስም፣ “ና ግባ፤ አንተ ጥሩ ሰው ስለሆንክ መልካም ዜና ይዘህ ሳትመጣ አትቀርም” አለው።